በአንድ ዓመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የተማሪዎች ምርቃት፤ ሰኔ 4 ቀን 2015 ዓ.ም አጋርፋ ለፌደራል ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ የሆነው የአጋርፋ የግብርና ኮሌጅ 525 ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡ ተማሪዎቹ ከአላጌ ግብርና ኮሌጅ ወደ ኮሌጁ ተዛውረው ሲማሩ የነበሩ ናቸው፡፡ ምርቀት ስነስርአቱ በከፍተኛ ድምቀትና የተለያዩ የኪነ ጥበብ ስራዎች ተከናውኗል፡፡በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የዋንጫ ፤የሜዳልያና የመፅሃፍት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የምርቃት ስነስርዓቱ ላይ “በቆይታችሁ መልካም ሥነምግባር አሳይታችሁናል፤ የምዘና ውጤታችሁ 97% በመሆኑ ኮርተንባችኋል” ያሉት የኮሌጁ የትምህርትና ስልጠና ም/ዲን አቶ አብርሃም ተስፉ ሲሆኑ፤ የዋንጫና የስራ ስምሪት የሰጡት የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ጫላ ፈዬራ” በሰለጠናችሁት ሙያ ስራ መፍጠር አለባችሁ፤የተለያዩ አይነት ገቢ ማስገኛ ስራዎች ላይ መሳተፍ አለባችሁ፤ያለ አዛዥ ለራሳችሁ ዝቅ ብላችሁ ህዝባችሁን ማገልገል አለባችሁ ፤ በረከትና ምርቃት በሚስገኝ የበጎ አድራጎት ስራ ላይመሳተፍ አለባችሁ“ በማለት ለተመራቂዎቹ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡ተመራቂዎችም ስለተደረገላቸውእንክብካቤ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Leave a Comment