አጋርፋ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምርትና ሥልጠና ኮሌጅ በ2015 በጀት ዓመት በተዘጋጀው አዲሱ ዕቅድ ላይ ህዳር 14 ቀን 2015 ዓ.ም የግማሽ ቀን ውይይት ተደረገ፡፡በዚሁ የኮሌጁ ዕቅድ ላይ የኮሌጁ ም/ዲኖች፣ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች የተሳተፉበት ሲሆን መድረኩን የመሩት የቴክኖሎጂ ብዜትና ሽግግር ም/ዲንና የኮሌጁ ዲን ተወካይ አቶ ፍራኦል ኤዴኦ ፕሮግራሙን በይፋ ሲከፈቱ ይህን ዕቅዱ የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር እስከ ፈፃሚው የሚወርድ መሆኑን በማሳሰብ ዕቅዱ አስተያየት ተሰጥቶበት ለሚመለከተው እንዲቀርብ የኮሌጁ የዕቅድ፣ዝግጅት ክትትልና ግማገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መማር አድማሱ እንዲያቀርቡ አድርገዋል፡፡
ከዚሁም ጋር ተያይዞ በየጊዜው በሚቀርበው የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት አቀራረብ ፕሮግራም መሠረት ወቅታዊ ሪፖርት ለሚመለከተው የሥራ ሂደት ባለቤት እንዲቀርብ የተገለፀና የተሰሩ ሥራዎች በተገቢው በተቀናጀና በተደራጀ ሁኔታ መቅረብ እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
በመጨረሻም በዕለቱ በቀረበው በአዲሱ ዕቅድ ገለፃ ላይ በተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች የኮሌጁ የዕቅድ ዝግጅት፣ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር አቶ መማር አድማሱ ምላሽ ከሠጡ በኃላ የቴክኖሎጂ ብዜትና ሽግግር ም/ዲንና የኮሌጁ ዲን ተወካይ አቶ ፍራኦል ኤደኦ ሰፋ ያለ ማብራሪያ በመስጠት በየዘርፉ የሚገኙ በየደረጃው ያሉ የሥራ ኃላፊዎች ዕቅዱን ወደራሳቸው በማውረድና በሥራቸው ለሚገኙ ፈፃሚዎች በማውረድ ሥራዎች በታቀደው ዕቅድ መሠረት እንዲከናወንና የተሠሩ ሥራዎች ሳይሸራረፉ በጥራትና በተቀመጠው ሪፖርት ማቅረቢያ ጊዜ በአግባቡ እንዲቀርብ አስገንዝበዋል፡፡
Recent Comments